Con5 tikur anbesa nigd 3

Con5 tikur anbesa nigd 3


የግንባታ ስራ ጨረታ
1. ጥቁር አንበሳ ንግድ አክሲዬን ማህበር ሊያሰራ ላስበው በ3000 ካሬ ሜትር የመሬት ይዞታ ላይ የሚያርፍ P2B+SB+G+11+Terrace ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንፃ መሉ የግንባታ ሥራን ከነሙሉ ግብአቶች ግልፅ በሆነ ጨረታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

2. ሥራውን ለመስራት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች ሟሟላት ይኖርበታል፡፡

2.1 BC/GC-1 ከኮንስታራክሽን ሚኒስቴር ለ2012 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ
2.2 ለ2012ዓ,ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ
2.3 ከሚመለከተው አካል የቀረጥ ክሊራንስ ማረጋገጫ
2.4 የቫት ምዝገባ ስርተፊኬት
2.5 መብቱ በህግ ከተሰጠው የመንግስት ተቋም በአቅራቢነት የተመዘገበ /Registered Supplier/
3. ተጫራቶች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት በአካል ቀርበው ብር 1000 በመክፈል የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቶች የግንባታ ሥራው የሚሰራበትን ቦታ (ሳይት) ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር(10) ቀናት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት መጎብኘት ይችላሉ::

5. ተጫራቾች “የቴክኒካል ፕሮፖዛል ከነኮፒው እና የጨረታ ማስከበሪያ” በአንድ ወገን፤ “የፋይናንሺያል ፕሮፖዛል ከነኮፒው” በሌላ ወገን በማድረግና ሁለቱንም በአንድ ኢንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 600,000) CPO ወይም የባንክ ማስተማመኛ ማቅረብ አለባቸው::

7. ተጫራቾች ስለ ጨረታው የበለጠ ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ፡፡

8. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በሃያ አንደኛው (21) ቀን (Calendar Days) ከቀኑ በ8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8 ፡30 ሰዓት ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ጥቁር አንበሳ ንግድ አክሰዩን ማህበር

ጂኦ ትራኮን ህንፃ 4 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 411

ስልክ ቁ. 09 11 09 62 99/ 0911207219

ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ተክስሐይማኖት ቤ/ ክ

የሚወስደው መንገድ ሜዳ ጋራዥ ፊት ስፌት ኦይል ሊቢያ

ማድያ አጠገብ

አዲስ አበባ

ማሳሰቢያ፡- ጥቁር አንበሳ ንግድ አክሰዬን ማህበር ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።



Posted: ሪፖርተር ግንቦት 09 ቀን 2012
Deadline: June 7, 2020


© walia tender

Report Page