Con mizan gibrena coll 2

Con mizan gibrena coll 2


የጨረታ ማስታወቂያ

በሚዛን ግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጅ ባለቤትነት በ2012 ዓ.ም የበጀት ዘመን ሊያሰራ ላሰበው የወተት ላም እርባታ ሼድ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቶችን ማሰራት ይፈልጋል።

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ 7/GC/BC እና በላይ የሆነ።
ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት ዋናውን ለማቅረብ በሚዛን ግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጅ ፋይናንስ እና በጀት ዳይሬክቶሬት የቢሮ ቁጥር የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300 ብር በመክፈል መግዛት ይጠበቅባችኋል።
የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 ( ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ (ለ128 ቀናት) ማቅረብ የሚችል።
ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ለእያንዳዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ በማቅረብ የፋይናንሻል እና የቴክኒካል ዶክመንቱን በጥቅሉ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለባቸው።
እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም መመታት እና መፈረም አለበት።
ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቶች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር እለበት።
እያንዳንዱፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፣ የተቋራጩ አድራሻ እና የተወካዩን ስልክ ቁጥር በመግለጽ መጻፍ አለበት።
ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ የፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት እለባቸው።
ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22 ተኛው ቀን በሚዛን ግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጅ ፋይናንስ እና በጀት ዳይሬክቶሬት የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል።
ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22 ተኛው ቀን በሚዛን ግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጅ ፋይናንስ እና በጀት ዳይሬክቶሬት ከሰዓት በኋላ 8 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
በሚዛን ግብርና ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ ኮሌጅ




Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 13 ቀን 2012

Deadline: June 10, 2020


© walia tender

Report Page