Con lideta

Con lideta


የግንባታ ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር con/001/2012
በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸው የግንባታ ሥራዎች በጨረታ መሳተፍ ለሚፈልጉ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች የተሟላ የሰው ኃይልና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች ለማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

ለሥራው ሕጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ ተጫራቾች የመስተዳድሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣
ከመንግሥት ግዥ ንብረት ማስወገጃ ኤጀንሲ (የኣቅራቢነት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዘር መግለጫ ሰነድ
ከሎት 1 እስከ ሎት3 የተጠቀሱ ፕሮጀከቶች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት፤
ከሎት4 እስከ ሎት6 የተጠቀሱ ፕሮጀክቶች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከአንድ ቀን በኋላ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት፤
ከሎት7 እስከ ሎት9 የተጠቀሱ ፕሮጀክቶች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሁለት ቀን በኋላ ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት፤
ከሎት10 እስከ ሎት 13 የተጠቀሱ ፕሮጀከቶች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከሦስት ቀን በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሁሉም ሎቶች የተጠቀሱትን ፕሮጀከቶች ሰነድ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ) በመክፈል በልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ሕንፃ አራተኛ ፎቅ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በምህንድስና ግዥ ቡድን ክፍል በመምጣት ሰነዱን በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የወሰዱትን ሰነድ ሲመልሱ የቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጂናል ከሁለት ኮፒ እና የፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጂናል ከሁለት ኮፒ ጋር በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ የታሸገውን ስድስት ኤንቨሎፕ በአንድ እናት ኤንቨሎፕ በሰም አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ሰነድና ኤንቨሎፕ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

5 ዋጋ (rate ) ያልተሞላለት የሥራ ዝርዝር እንዲሁም የሥራ ዝርዝር ዋጋ rate) ላይ ድልዝ ስርዝ እና ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡

6. ተጫራቾች ለመወዳደር ያቀረቡት ዋጋ ሦስት ፐርሰንት (36) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond or bid security) ወይም በባንክ ትዕዛዝ ሲፒኦ (qpp) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE) ከታወቀ ባንከ ለልደታ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ስም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በልደታ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8 መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

9 ጨረታው በተጠቀሰው ቀን፤ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

10. አሰሪው መስሪያ ቤት አሸናፊው ካሸነፈበት አጠቃላይ ሥራ 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡

11. በተጨማሪም የትኛውም ከላይ የተዘረዘሩትን ሆነ በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማክበር በሚያስገቡት የጨረታ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገፆች ላይ ማህተምና ፊርማ አለማድረግ፤ በሥራ ዝርዝር በሙሉም ሆነ በአንድ የሥራ አያትም ላይ ዋጋ አለመሙላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ

ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ስፌት ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ላይ አራተኛ ፎቅ ኮንስትራከሽን ጽ/ ቤት የምህድስና ግዥ ቡድን ክፍል፤

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ ልደታ ክ/ ከተማ ኮንስትራክሽን


Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 29 ቀን 2012

Deadline: May 27, 2020


© walia tender

Report Page