Con gedio zon repi w fin1

Con gedio zon repi w fin1

Walia Tender

በድጋሚ የወጣ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የጌዴኦ ዞን የረጲ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በረጴ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ለማስገንባት በግንባታ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት፦

1. GC /BC 5 እና ከዚያ በላይ፡፡

2. በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዘገቡና በ2012 ዓ.ም. የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡

3. ከመንግሥት የሚፈለግበት የግብርና የታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ለበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከታክስ አስተዳደር ቢሮ ማቅረብ የሚችል፡፡

4. ወርሃዊ የታክስ ማስታወቂያ በማቅረብ የሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከታቸው ገቢዎች ጽ/ቤት የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡

በክልሉ የግንባታ ሥራ ላይ ተሰማርተው የመልካም ስራ አፈፃፀም ያላቸውና ስራዎችን ያላስተጓጎሉ፣ውል ያላቋረጡ ተቋራጮችን እየጋበዘ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተቋራጮች የማይመለስ ብር 300.00/ ሦስት መቶ ብር ብቻ / በኘሮጀክቱ ስም ለጌዴኦ ዞን ረጲ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ገቢ በማድረግና ደረሰኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ይዘው በመቅረብና በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ የጨረታውን ሰነድ ከጌዴኦ ዞን ረጲ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሠነዶቻቸውን በመሙላት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ አድርጎ በኤንቨሎፕ በማሸግ በእያንዳንዱ ላይ ማህተሙንና ፊርማውን በማሳረፍ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ ሰነድ እያንዳንዱን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 10 ኛው ቀን 4 ፡ 00 ሰዓት ድረስ በረጴ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
በኦርጅናል ሰነድ ላይ የሚደረግ ማናቸውም ስርዝ ድልዝ በሚነበብ መልክ በድጋሚ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 ( አንድ መቶ ሺህ ብር ) በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፤ በጥሬ ገንዘብ፣ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ጨረታው በውክልና የሚመጡትን አይመለከትም፡፡
በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡

ጨረታው የሚዘጋው 10 ኛው ቀን በ 4 ፡ 00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና የሚመለከታቸው ክፍሎች በተገኙበት በዚሁ ቀን በ 4 ፡ 30 ሰዓት ከረጴ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይሆናል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሳያሟላ የሚያቀርብ የሥራ ተቋራጭ ከጨረታው ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡09 16-44-4677/ 09 45-6324 47

የጌዴኦ ዞን የረጲ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት



Posted: ሪፖርተር ግንቦት 26 ቀን 2012

Deadline: June 12, 2020


© walia tender

Report Page