Con gc bc 5 aa arada kk

Con gc bc 5 aa arada kk


ግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 07/2012

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ሊያስገነባቸው የፈለገውን ስራ የሚሠሩ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ።

በዘርፉ 2012 የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ሆነ አማካሪ ከመስተዳድሩ ኮንስትራከሽን ቢሮ ተመዝግቦ የብቃት ማረጋገጫ ወይም የአጭር ምዝገባ ሰርተፍኬት ሳይዝ በሴክተሩ መሳተፍ አይችልም።

ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር / በመከፈል በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት 3ተኛ ፎቅ ቀርበው በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond 70,000 ብር ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ለ90 ቀናት የሚያገለግል ሆኖ ከኦሪጅናል ቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት።

በተጨማሪነት ስራውን በምን ያህል ጊዜ እንደሚያጠናቅቁ የሚገልጽ የስራ መርሃ ግብር /ወርክ ስኬጁል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 6 ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱንና የተወዳደሩበት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

ተቋራጮች የስራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኤንቨሎፕን በሰም በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ስዘኛው ቀን በአራዳ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት ይህም ከሆነ ተጫራቹ ያስገባው ሰነድ ውድቅ ይሆናል ።

ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በወጡና በሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች ላይ ተቋራጭ ከአንድ በላይ ጨረታ መሳተፍ አይቻልም፡፡

***ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። *

ጨረታውን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ይከፈታል የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪይ ኸረስት የአራዳ ክስ ኮንስትራክሽን ጽ/ ቤትምህንድስና ግዥ ቡድን በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ፡

የአራዳ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ ቤት


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 21 ቀን 2012

Deadline: June 12, 2020


© walia tender

Report Page