Con bc 4 ad ethiospace 2

Con bc 4 ad ethiospace 2


የግንባታ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ብ/ ግ/ ጨ/ESST/04/2012

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በእንጦጦ ኦብዞርቫቶሪና ምርምር ማዕከል

የአንቴና ፋውንዴሽን ግንባታ
የሰኪዩሪቲ ካምፕ ግንባታ
የግምጃ ቤት ግንባታ
የወርክ ሾፕ ግንባታ ለማሰራት ደረጃ 4 BC እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት

ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ እና ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ግዢ ሲመጡ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል በኢንስቲትዩቱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 100,000.00 ( አንድ መቶ ሺ ብር) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢንስቲትዩቱ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
የጨረታ መክፈቻ ቀን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ21 ተካታታይ ቀናት በሁዋላ ባለው መጀመሪያ የስራ ቀን ከረፋዱ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር በአቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደ አስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ

አዲስ አበባ ጉለሌ ወረዳ 2 ፣ የቤት ቁጥር 179

የስልክ ቁጥር : 011-872-0257

ምስካየ ሀዙናን ቤተክርስትያን ፊት ለፊት ወደ መነን በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ህንፃ

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 05 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page