Con addis city meskel7

Con addis city meskel7


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር የተ / አ / አ / የአ / ል / ግ /04/2012
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተፋሰስ እና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ከአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እስከ መስቀል አደባባይ ድረስ ያለውን ቦታ የአረንንዴ ልማት ግንባታ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 GC ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች:-

የዘመኑ የታደሰና በመስኩ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ስራ ምዝገባ ምስክር ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተፋስስና አረንንዴ አንባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአካል በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን፤ እየገለፅን አድራሻችን 4 ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል በስተጀርባ ፖስታ ቤት ያስገነባው ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ኮፒ ሁለት እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ኮፒ ሁለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ16 ኛው የስራ ቀን እስከ ጠዋት 4 ፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጁት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ CPO ብር 500,000/ አምስት መቶ ሺህ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ 16 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተፋሰስ እና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ዥ ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል፡፡
ጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይቶ ውል እስኪፈፅሙ እንደተያዘ ይቆያል፡፡
የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ሰነድሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-558-11-79 ደውለው ይጠይቁ፡፡
ኤጀንሲው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተፋሰስ

እና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት እና

አስተዳደር ኤጀንሲ

አዲስ አበባ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 13 ቀን 2012

Deadline: June 11, 2020


© walia tender

Report Page