Con 6

Con 6


የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት በጂንካ ከተማ ከዚህ ቀደም የግንባታ ሥራው ተጀምሮ የተቋረጠውን G+3 የቢሮ እና G+0 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ህንፃ ግንባታን በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቶችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሠረት:-

ደረጃ አራት እና ከዚያ በላይ ጠቅላላ ወይም ህንፃ ሥራ ተቋራጭ የሆነ፡
በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ወይም በክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራሽን ቢሮ ተመዝግቦ ለ 2012 የበጀት ዓመት ከላይ በተራ ቁጥር አንድ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው
ለ2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው ፣
የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ ለ2012 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ Nalid tax clearance certificate for 2012 E.C budget year/
በፌዴራል ወይም በክልሉ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠበት የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ / Registered on FPPA or PPA Suppliers List /
ከዚህ ቀደም በዞኑ የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራ ውሎችን በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረክብ ለመሆኑ የግንባታ ጥራት ማጓደል ማዘግየት ውል ማቋረጥ ወዘተ የውል አስተዳደርና አፈፃፀም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠው ከሚመለከተው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር የመንግስት አካል ማስረጃ ያለው በመሆኑም ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ በግንባታው ወይም በፕሮጀክቱ የውል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአስሪው ባለበጀት መ/ቤት በወቅቱ ያላስረከበ ውል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጭ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ሲቀርቡ ይህን ማስረጃ ካላቀረቡ የጨረታ ሰነዱን መግዛት አይችሉም፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከዋለበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 30 /ሰላሳ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጂንካ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ክፍል የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው በመሳተፍ መወዳደር ይችላል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ 150,000 / አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ/ ብር ከታወቀ (ስልጣን ከተሰጠው) ባንክ ወይም የፋይናንስ ተቋም በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ ከጨረታው ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ ስሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በቴክኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሽግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚህ ጨረታ ሥራ በተዘጋጀ ፤ ሳጥን ውስጥ በሰላሳ አንደኛው /31 ኛው ቀን የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ 3 ፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡30 ሰዓት ድረስ ሙግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚህ ዕለት 6:30 ሰአት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8 ፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡ ፡ የጨረታው አከፋፈት ሥነ ሥርዓትም በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኋላ ፋይናንሽያል ዶክመንት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ ፡ መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-046-775 0256 ወይም 046-77523-24 በመደወል መረዳት ይችላሉ።
በደ/ ብ/ ብ/ ህ/ ክ/ መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር

የጂንካ ከተማ ፋ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት ጂንካ





Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 17ቀን 2012

Deadline: May 25, 2020


©walia tender

Report Page