Con 56

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002C/2012
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ ከታች የተዘረዘሩትን የግንባታ ስራዎችን የሚሰሩ የተለያየ ደረጃ ያላቸውን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ ፍቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፣ ወቅታዊ ታክስ ክሊራንስ የሚያቀርቡ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ የአጭር ምዝገባ ላይ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት 1 ጂ+2 የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የመጀመሪያ ደረጃ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት (GC 5/BC 4 እና ከዚያ በላይ).
ሎት 2 ንፋስ ስልክ ቴ/ሙያ ትምህርት ስልጠና (GC5/BC 4 እና ከዚያ በላይ)
ሎት 3 ሀገር ፍቅር ቲያትር እድሳት ስራ(GC 5/BC 4 እና ከዚያ በላይ)
ሎት 4 3ቢ+ጂ+15 የጤና ቢሮ ህንፃ (ICB_GC1/BC1)
ሎት 5 አቃቂ ስፖርት ሜዳ (GC 6 እና ከዚያ በላይ)
ሎት 6 ቂርቆስ ወረዳ 2 አስተዳደር ህንፃ (GC 5/BC 4 እና ከዚያ በላይ)
ሎት 7 ጃን ሜዳ ጅምናዝየም (GC 2/BC 1 እና ከዚያ በላይ)
ሎት 8 አዲስ ብድር እና ቁጠባ (GC 5/BC 4 እና ከዚያ በላይ)
ሴቶች እና ህፃናት ቢሮ ቀጨኔ መድሀኒአለም (GC 4/BC 3 እና ከዚያ በላይ)
ጎሮ ፖሊስ ሊፍት እና ጀነሬተር (GC 5/BC 4 እና ከዚያ በላይ)
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ቀን ድረስ የማይመለስ 500.00 / አምስት መቶ ብር / በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በሰም በማሸግ የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ኛ ቀን 4 ፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን (Technical & Financial Proposal ) ለእያንዳንዱ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3.የቅድመ ብቃት ጨረታ ሰነድ (Technical proposal ) በዚህ ዕለት በ 4 ፡ 45 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ 8ኛ ፎቅ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሠረት በባንክ ክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው::
5. ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ መሳተፍ አይችሉም
6. የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ:- የጨረታ መክፈቻ 21 ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ
አዲስ አበበ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 24 ቀን 2012
Deadline: May 22, 2020
© walia tender