Con 4 kirkos

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቂ/ ቤ/ ል/ ግን/ ግብ/002/12 እና የቢ/ እቃ/017/12
የቂርቆስ ቤቶች ልማት ፕ/ቅ/ጽ/ቤት በጨረታ መለያ ቁጥር ቂ/ቤ/ል/ግን/ግብ/002/12 በቦሌ አራብሳ 5 የግንባታ ሳይት ላስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤትና የሕንጻ (ብሎክ) ቁጥር በጨረታ አወዳድሮ በላሜራ ብረት ማሠራትና ማስገጠም በተጨማሪም በጨረታ መለያ ቁጥር የቢ/እቃ/017/2012 ቋሚ እቃ /የላተራል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁና በጨረታው ለመካፈል የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሠረት ቀርባችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የሚያቀርቡ፤
የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣
የግብር ከፋይነት ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነታቸውን ማረጋገጫ የሚያቀርቡ፤
በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ በአቅራቢነት ምዝገባ በዌብ ሳይት (በድረ-ገጽ) የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
ጨረታ ለመሳተፍ ከግብር እዳ ነፃ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፤
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለምትጫረቱበት ጥቅል የእቃ ዋጋ ሁለት በመቶ (2%) በCPO ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር ) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይኖርባቸዋል፤
ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በተቀመጠው ስፔስፊኬሽን እና ጥራት መሰረት ናሙና (Sample) በማዘጋጀት ቦሌ አራብሳ 5 ቂርቆስ ቤቶች ልማት ቅ/ጽ/ቤት የግዥ ዕቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሚያስገቡበት ጊዜ ተፈላጊ ሰነዶችን (ቴክኒካል ዶክመንቶችን) በቴክኒካል ፖስታ እና የሚወዳደሩበትን ዋጋ (ፋይናንሽያል) ዶክመንቶቹን ደግሞ በፋይናንሽያል ፖስታ ውስጥ በማድረግ እና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማኅተም አርፎበት የቴክኒካል ፖስታውን ቴክኒካል ፖስታ እንዲሁምፋይናንሻል ፖስታን ደግሞ ፋይናንሻል ፖስታ ብሎ በመለየትና በመፃፍ በሁለት በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ( አስር ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ ( ቅዳሜ እንደ አንድ የሥራ ቀን ይቆጠራል) ዘወትር በሥራ ሰዓት በቅ/ፅ/ቤቱ የግዥ ዕቅ/ዝግ/አፈ/ደ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ጨረታው በ 11 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡ 00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4 ፡ 30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦሌ አራብሳ 5 በቂርቆስ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የግዥ እቅድ ዝግጅት አፈፃፀም ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የበዓል ( የዕረፍት ቀን ) ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተገለፀው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፦በስልክ ቁጥር 011-26-50-78 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የቂርቆስ ቤቶች ልማት ፕ/ ቅ/ ጽ/ ቤት
Posted:አዲስ ዘመን ሚያዝያ 30 ቀን 2012
Deadline: May 22, 2020
© walia tender