Con 4 kazza 19

Con 4 kazza 19


የማጠናቀቂያ የግንባታ ሥራ /Finishing Works/
ጨረታ ማስታወቂያ
ካዛ የገበያ ማዕከል እማ ካዛንቺስ አካባቢ ባለው ይዞታ ላይ ለሚያሠራው ሁለገብ /2B+G+12/ ህንፃ” የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት የመጀመሪያ ዙር ማጠናቀቂያ ሥራውን ማለትም (2B+G+5) የህንፃውን ክፍል ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራውን /Finishing Works/ ለመስራት የሚችሉ፡

ደረጃ BC/GC-3 እና ከዛ በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮች የ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ የቲን ሰርተፍኬት ኦርጅናል ከኣንድ ፎቶ ኮፒ ጋር በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የካሌንደር ቀናት ከአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1,000.00 / አንድ ሺ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ በአክሲዮን ማህበሩ ስም ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሺ / በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /CPO/ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /Unconditional Bank Guarantee/ ለ60 ቀናት የሚያገለግል ሆኖ ከቴክኒካል ሰነዳቸው ጋር ለብቻው በፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ስራቸውን የሚሰሩበትን የጉልበት፣ ኢኩፕመንትና ማቴሪያል ዋጋቸውን በጥልቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት የፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸውን ከአንድ ኮፒ ጋር በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ፣ እንዲሁም የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን ኦርጅናል ከአንድ ከፒ ጋር በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ፣ የጨረታ ማስረከቢያ Bid Bond/ ለብቻው በኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ፣ እንዲሁም ጠቅላላ ስነዳቸውን በአንድ ላይ በሌላ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሚቆጠር 22 የካሌንደር ቀናት /Calendar Days/ እስከ ጠዋቱ 5 ፡30 ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከላይ ከተመለከተው ሰዓትና ቀን ዘግይተው የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም::
ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 7 ፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ ቤት ይከፈታል።
አክስዮን ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አክስዮን ማህበሩ አድራሻ፡ - ኡራኤል አካባቢ ሙሉጌታ የገበያ ማዕከል ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 623
ስልክ፡ 0911-133954 /0911-193563
አዲስ አበባ



Posted: ሪፖርተር ግንቦት 09 ቀን 2012
Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page