Con 4

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 17/2012
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ በአነስተኛ መስኖ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት በመደበኛ በጀት በክልላችን ግድብ በሚሰራባቸው ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የማሶነሪ ግድብ በር ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል።
በዘርፉ እና ለዘመኑ የታደሰ ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የቫት ተመዝጋቢነት ሰርቲፍኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የዕቃው አይነት የአምራቹን ሥም፣ የተመረተበትን ሀገር እና የሞዴል ቁጥር በዝርዝር መግለጫው (Specification) መሠረት ካታሎግ (Catalogue) ማቅረብ የሚችል።
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ የግብዓት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋ ስትና ብር 12,000.00 የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ፣ በሁኔ ታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ ሰማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና፣ ጥሬ ገንዘብ ወይም የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ለስድስት ወር ማስያዝ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአራት በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቶች ሁለቱ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ፣ በማለት በታሸገ ፖስታ በግብርና ቢሮ የግብርና ግብአትገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡,
በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ን የማይመለስ ብር 50.00 / ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታው ማ ስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ መ/ቤቱ ወይም ጽ/ቤት በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሠዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ቢሮ የግብርና ግብዓት ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 018 በ16 ኛው ቀን 2012 ዓ. ም 4 ፡30 ሠዓት ይከፈታል፡፡
ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 21 ድረስ በአካል ወይም በፋክስ ቁጥር 0582208771/ በመላክ፣ በስልክ ቁጥር 0582205849/7048 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ መከታተል ይቻላል፡፡
የጨረታውን ማስታወቂያ በቢሮው ድረ-ገጽ web site Address/ www.amhboard.gov.et መከታተል ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ግብርና ቢሮ
ባህር ዳር
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 22፥2012
Deadline: May 15, 2020
© walia tender