Con 4

Con 4


የጨረታ ማስታወቂያ
የካፋ ዞንፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ከዞኑ ጤና መምሪያ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጀት ድጋፍ በዴቻ ፣ በጊምቦ ፣በቢጣ እና ጨና ወረዳዎች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች የውሃ ሲቪል ግንባታና ስራ ለማሰራት እንዲሁም ከዞኑ ማዕድን ኤነርጂ ልማት መምሪያ በቀረበለት ጥያቄ በጎባ ወረዳ ሻዳ ቀበሌ የመጠጥ ውሃ ሲቪል ግንባታና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ለማሰራት ጨረታዎችን በሎት በመከፋፈል በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኦሪጂናል እና የማይመለስ ኮፒ ዶክሜንት ጨረታውን ሊገዙ ሲመጡ ይዘው በመቅረብ ማመሳከር አለባቸው፡፡

ሎት 1. በጨና ወረዳ ሼቻ ጤና ጣቢያ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲቪል ግንባታ ስራዎች
ሎት 2. በዴቻ ወረዳ ሞዲዮ ጤና ጣቢያ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲቪል ግንባታ ስራዎች
ሎት 3 በጊምቦ ወረዳ ዝንጋጅ ጤና ጣቢያ ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ
በቢጣ ወረዳ ኦዳ ጤና ጣቢያ ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ
ሎት4 . በጎባ ወረዳ ሸዳ ቀበሌ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲቪል ግንባታና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች በድጋሚ የወጣ ተጫራቾች ለሎት 1. ለሎት 2. እና ለሎት 4. በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ደረጃ G.C.W.W.C/ W.W.C-6 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል።ለሎት 3. መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ደረጃ B.H drilling level -3 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 / ሶስት መቶ/ ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ካፋ ዞን ፋይናንስና ኢ/ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለሎት 1. በባንክ የተረጋገጠ 40,000 / አርባ ሺህ ብር / ለሎት 2 .40000 / አርባ ሺህ ብር/ ለሎት 3. 40,000/ አርባ ሺህ ብር ለሎት 4. 40,000 / አርባ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO/certified Bank order / በካፋ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ስም በማሠራት ከኦሪጂናል ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መጫረት አይችልም፡፡
ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል የጨረታ ዶክሜንት ሲመልሱ ተገቢውን ፊርማ እና ማህተም በማሳረፍ ለየብቻ አንድ ኦሪጂናል እና ሶስት ኮፒ የተሟላ ሰነድ በሰም /በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
የጨረታው ሳጥን በ 22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 3 ፡ 30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ዝግ ወይንም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የአቅራቢነት ምዝገባ የቲን የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኮፒ ዶኪሜንት ከቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
ተጫራ ቾ ች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ / performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት / የስራ ቀናት ውስጥ ከአሰሪው መ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም አለበት፡፡
ተጫራቾች አሰሪው መ/ቤት ያዘጋጀውን የቴክኒካል ዶክሜንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 33 11 826 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የካፋ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

ቦንጋ


Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21 ቀን 2012
Deadline: May 20, 2020


©walia tender


Report Page