Con 34

Con 34


ለ መጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድርጎት ድርጅት ጽ/ቤት በዲላ ከተማ ሲሆን ከቻይልድፈንድ ኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ በወናጎ ወረዳ ወናጎ ጤና አጣቢያ የእናቶች ማቆያ እና በዲላ ዙሪያ ሚችሌ ሲሶታ ጤና አጣቢያ የእናቶች ማቆያ እድሳት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ቢያንስ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

የታደሰ ህጋዊና ከሙያው ጋር የተያያዘ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
የታደሰ የዋና ምዝገባ ፈቃድ እና የወቅቱን ግብር የከፈሉ
የቲን ቁጥር/ግብር ከፋይ የምዝገባ ወረቀት/ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ
ቫት ምዝገባ ወረቀት/ ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ
ደረጃ ቢሲ/ጂሲ 7 እና ከዚያ በላይ የግንባታ ፈቃድ ያለው
በጨረታው ከሚሰራው ስራ ጋር በተያያዘ ከሁለት ዓመት ወዲህ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ምስክር ወረቀት ከታወቀ ድርጅት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ግንባታው የሚያካትታቸውን ዝርዝር ሥራዎች Specification/ ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 6፡30 እና ከ7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ዲላ በሚገኘው ባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ጽ/ቤት ሂሣብ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 1% ሲፒኦ በባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ስም በማሰራት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የድርጅታዊ ፕሮፋይላቸውን ኮፒ ለየብቻው ከሲፒኦ ጋር በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጐት ድርጅት ጽ/ቤት ጨረታው ከወጣበት ከሰባተኛው/7 ኛው/ ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2 ፡30 እስከ 6 ፡30 ድረስ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ በ8 ፡00 ሰዓት ዲላ በባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጐት ድርጅት ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁ መረጃዎችን ቢፈልጉ ወይም ተጨማሪ ማብራሪያ ሲያስፈልግ በስልክ ቁጥር፡- 046-331-00-49 ወይም 046-331-42-33 ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ባሳያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድርጎት ድርጅት

_______________________________
Category : Construction and Construction Machinery, Construction Service and Maintenance, House and Building Construction

Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 17 ፥2012
Deadline :2020-04-03

Report Page