Con 33

የህንፃ ጥገና ግልፅ ጨረታ
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ምስራቅ ሪጅን (አዳማ) በአርካይቭ ክፍል ስራ ግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/ BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 07 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግና ፋሲሊቲ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለ ስ ብር 50.00 ( ሃምሳ ብር በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጨረታው መጋቢት 18ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 07 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፤
ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 10,000.00/ አስር ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 07 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 5 ፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፤
መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-1121660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ ቴሌኮም
ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
_______________________________
Category : Construction and Construction Machinery, Construction Service and Maintenance, House and Building Construction
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 17 ፥2012
Deadline :2020-04-15