Con 29 et ele powr 29

Con 29 et ele powr 29


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/01/2012

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በግልገል ጊቤ 2ኛ ኃይል ማመንጫ ለሰራተኞች የሚያገለግል መኖሪያ ቤት ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡ የኃይል ማመንጫ ጣቢያው የሚገኝበት ቦታ ከአዲስ አበባ 265 ርቀት ያለው ሲሆን 200 ኪ.ሜ አስፓልት እና 65 ኪሜ ፒስታ መንገድ ነው፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

በደረጃ GC/BC-1 ደረጃ ያላቸው ህጋዊ የስራ ተቋራጮች፡፡
ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ በስራ ተቋራጮች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ኬኬር ህንጻ 1ኛ ፎቅ ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 ( ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የግንባታ ስራ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/01/2012 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦርጂናል እና 2(ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የጠቅላላ ስራውን ቫትን ሳይጨምር 1% ( አንድ ፐርሰንት) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀን የሚቆይ ተቀባይነት ያለው የባንክ ክፍያ ትእዛዝ(CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
ጨረታው ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 28 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቶች መረጃ ከፈለጉ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ኬኬር ህንጻ 1ኛ ፎቅ ጀነሬሽን ኦፕሬሽን ግዥ ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-5 581916/1725 መደወል ይችላሉ ::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page