Con 2 defence cons24

Con 2 defence cons24


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE ፕሮ/11-10B/42/2012

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የ Toilet door Closer አቅርቦትና ገጠማ ስራ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

ስለሆነም፡

ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ/ በመክፈል ቅዳሜን ጨምሮ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ጦር ሀይሎች ፊት ለፊት በምድር ሀይል ግቢ ውስጥ ባለው ቢሮአችን ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ::
የጨረታ አሽናፊው ወደ ስራው ሲገቡ የውለታው 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስያዝ ይጠበቅባቸኋል::
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 8 ፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ጨረታው ግንቦት 19/2012 ዓ. ም ከቀኑ 8 ፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ኃይል ግቢ ውስጥ በሚሰራው ህንፃ ፕሮጀክት መምጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118-49 38 23 ይደውሉ::


Posted: ሪፖርተር ግንቦት 02 ቀን 2012
Deadline: May 27, 2020


© walia tender

Report Page