Con 2

የጨረታ ማስታወቂያ
የግዮን ሆቴል ድርጅት የሣባ አዳራሽ ግንባታ ሥራን ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
የ2012 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
Tin No. /የግብር መለያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
/Vat/ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
የታክስ ክሊራንስ 6 ወር ያልሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገበና የ2012 የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያለው፡፡
ደረጃ BC4/GC5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፡፡
ተጫራቾች በፌዴራል ግዥ እና የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኑ 125,000.00 / አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ፎርሞች ማሟላት የተጫራች ግዴት ሲሆን፤ ያልተሞላ የጨረታ ሰነድ ከውድድሩ የሚያስወጣ መሆኑን ተጫራቾች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታውን የሚያሸንፍ የሥራ ተቋራጭ ለሥራው ዋስትና 10 በመቶ Performance Bond/ እና የባንክ ዋስትና /Bank Guaranty/ ከባንክ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የጨረታው ሰነድ በግልፅ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ተለይቶ የቴክኒክ፣ የፋይናንሺያልና ሲፒኦ /ቢድ ቦንድ/ ሰነዶች ለየብቻቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻ፣ ቀን፣ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ታሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በሚያቀርቡት ኦርጅናል ሆነ ኮፒ ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ የዋጋ ንባብና በሂሳብ ማስተካከያ መሀል ያለው ልዩነት ከ2% መብለጥ የለበትም፡፡
የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ድረስ በድርጅቱ የግዥ አገልግሎት ቢሮ ድረስ መተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታውን ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ10 ኛው ቀን ከቀኑ በ8 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ በ8 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 5 51 32 22 Ext. 5429/5163 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2 ፡00-6 ፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7 ፡00-11 ፡00 ዓርብ ጠዋት ከ2 ፡00 - 5 ፡30 ከሰዓት ከ7 ፡30 – 11 ፡00
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የግዮን ሆቴል ድርጅት
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 21 ቀን 2012
Deadline: May 8, 2020
©walia tender