Con 2

Con 2


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፌ / ፖ / ኮ :-41/2012
የኢፌዴሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ለ2012 በጀት ዓመት ለተለያዩ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል በደጋሚ የወጣ የተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሥራው ጋር የተገናኘ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ወቅታዊ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በዌብሳይት ላይ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሠርተፍኬት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ፌ/ፖ/ኮ 4/2012 በድጋሚ የወጣ የተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች 23,000.00 ( ሃያ ሶስት ሺህ ብር) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (BID BOND) /CPO/በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፌ/ፖ/ኮ 4/2012 በድጋሚ ያወጣ የተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች እስከ 04/09/2012 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ የ ማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ዲቪዥን ቢሮ ቁጥር 203 ቀርበው የጨረታ ሠነዱን በመግዛት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማሸግና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ወይም በመልዕክት ሣጥን ቁጥር 199 መላክ ይችላሉ፡፡ መ/ቤታችን ስለጨረታ ሰነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት አይወስድም:: ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከላይ በተገለፀው የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ የመጨረሻ ቀን ከረፋዱ 4 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው በተመሳሳይ ቀን በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መ/ ቤት ትንሹ አዳራሽ በ4 ፡30 ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር 011-5-58-17-39/011-5-52-44 12/011-5-31-20-95/011-5-31-21-99 የውስጥ ስልክ 2104/1107/1101 ፋክስ ቁጥር 011-5-52-55 17 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢ. ፌ. ዴ. ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን


Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 18 ቀን 2012
Deadline: May 12, 2020


©walia tender

Report Page