Con 12
አርጂ ገበያ (ጨረታ ማስታወቂያዎች)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ለ2012 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተገለፁት ዝርዝሮች በግልፅ ጨረታ ቁጥር 06/2012 አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
BC-4 ወይም GC-4 እና ከዚያ በላይ
ስስዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራጮች
ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላው/ያላት፡፡
የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፡፡
ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፊኬት ያለው/ያላት፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ 100,000.00 (መቶ ሽህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ስለዚህ ይህ ጨረታ ከመጋቢት 12 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም በተከታታይ ባሉት አስራ አምስት (15) የስራና የበዓል ቀናቶችን ጨምሮ የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ደብረ ዘይት በሚገኘው አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዋናው በር በመምጣት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 7፡30 ሰዓት ላይ ደብረ ዘይት ከተማ በሚገኘው የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 4 33 84 03 ወይም 011 4 33 80 40 የውስጥ መስመር 1330/1446 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ
Categories
Construction and Water Works Maintenance and Repair
posted date:Addis Zemen ( መጋቢት 12፣ 2012 )
Dead line: April 06, 2020