Con 11

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE ፕሮ/11-10B/39/2012
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ውስጥ የተካተተው አዲሱ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተያያዥ ሥራዎች አገልግሎት የሚውል የRoad Sign and Pavement making ጨረታ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እቃውን ተጫራቹ አቅርቦ ለማሰራት ይፈልጋል::
ስለሆነም፡
ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ / በመክፈል ቅዳሜን ጨምሮ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ጦር ኃይሎች ፊት ለፊት በምድር ሀይል ግቢ ውስጥ ባለው ቢሮአችን ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ::
የጨረታ አሽናፊው ወደ ስራው ሲገቡ የውለታው 10% የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስያዝ ይጠበቅባቸኋል::
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ . ም ከጠዋቱ 5 ፡ 00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ጨረታው ግንቦት 4 ቀን 2012 ዓ . ም ከጠዋቱ 5 ፡ 30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
ተጫራቾች የሥራ ቦታውን በአካል በመቅረብ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ኃይል ግቢ ውስጥ በሚሰራው ህንፃ ፕሮጀክት መምጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
ለበለጠ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 0118-49 38 23 ይደውሉ::
Posted: ሪፖርተር ሚያዝያ 21 ቀን 2012
Deadline: May 12, 2020
© walia tender