Con 1

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ተጫራቾችን ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
A. የመንገድ መብራት “traffic light at Get Ishet & Hirna” በኤሌክትሮ መካኒካል ኢንጂነሪንግ ደረጃ - 4 እና ከዚያ በላይ ያላቸው፤
B. የቢሾፍቱ ከተማ ባህል አደራሽ G-C 4/ B.C 3 ያላቸው እና ከዚያ በላይ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉት አካላት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የማይመለስ ብር 300( ሶስት መቶ) ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በባንክ ሒሳብ ቁጥር 071 በቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ስም በማስገባት የገቢ ደረሰኙን ከቢሾፍቱ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን በመቁረጥ ከቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የግዥና ንብረት የሥራ ሂደት 2ኛ ፎቅ አስፈላጊውን መረጃ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በመያዝ እስከ 9/9/2012 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ብቻ መግዛት ይችላሉ::
ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር የጨረታ ማስከበሪያ (BID BOND) ለመንገድ መብራት “traffic light” ብር 75,000 ( ሰባ አምስት ሺህ) ለባህል አዳራሽ ብር 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guaranty) በመጫረቻ ሰነድ ላይ በሚጠየቀው መሰረት ማቅረብ አለበት፡፡
ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዱን በመጫረቻ ሰነድ ላይ በሚጠየቀው መሰረት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በኤንቨሎፑ ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ ሰነዱ ኦርጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመጻፍ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር የግዥና ንብረት የሥራ ሂደት 2ኛ ፎቅ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
ጨረታው በ9/9/2012 ዓ. ም ከሰዓት በኋላ በ8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ 8:30 ሰዓት በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 0114-30 1758 ደወለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የቢሾፍቱ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 18 ቀን 2012
Deadline: May 17, 2020
©walia tender