Con 08

የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን የሀደሮ ከተማ አስተዳደር የመ/ደ/ፍ/ቤት የቢሮ ግንባታ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡
ደረጃ GC/BC-7 እና ከዚያ በላይ፤
የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውንና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሰርተፍኬታቸውን በ2012 ዓ/ም ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስን የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300 / ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ዘወትር በስራ ቀናት ወደ ሀደሮ ከተማ አስተዳደር የመ/ደ/ፍ/ቤት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፣
ተጫራቾች ብር 100,000 / አንድ መቶ ሺህ ብር / የጨረታ ዋስትና በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ያልተመሠረተ ቢድ ቦንድ ከቴክኒካል ዶክመንት ጋር ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻው በማሸግ፤ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻው በማሸግና በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እና በማሸግ ጨረታው ከወጣበት በ 31 ኛው ቀን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ከጠዋቱ 5 ፡ 00-8 ፡ 00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
ጨረታው በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8 ፡ 00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ 30 ደቂቃ ይከፈታል፡፡ ቢሆንም ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ለሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር +251464320574
በደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን
የሀደሮ ከተማ አስተዳደር የመ/ ደ/ ፍ/ ቤት
_______________________________
Category : Construction and Construction Machinery, House and Building Construction
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 18 ፥ 2012
Deadline :2020-05-02