Comp other furn ssnp plan21

Comp other furn ssnp plan21


እስከ ግንቦት 17 ብቻ (only 5 days left) ታላቅ ቅናሽ!

የጨረታ ማስታወቂያ

01/2012

የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ፕላን ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ ለቢሮው የሚያስፈልጉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች

ኤሌክትሮኒክስ (ዴስክቶፕና ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ፤ ፕሪንተር እና ፋክስ ማሽን)
ሞተር ሳይክል ተሽከርካሪ
የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መሣተፍ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 09 በመምጣት የማይመለስ ብር 50 / ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ::
ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 / አምስት ሺ/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታ ሰነዱንም ያንዱን ዋጋ በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በ16 ኛው የስራ ቀን (16 ኛው የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል) ከጠዋቱ 4:30 እስከ 6:30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ::
ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት በ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ::
ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልጽ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በማህተምና በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
የመጓጓዣና እስከ ርክክብ ድረስ ያሉ ወጪዎች በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል ፡፡
ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0462126809

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የፕላን ኮሚሽን



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 9, 2020


© walia tender

Report Page