Comp bd costruction bur1

Comp bd costruction bur1


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የባህር ዳር ከተማ አስ/ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በአለም ባንክ በጀት በአቅም ግንባታ ከተያዘዉ Bahir Dar UIIDP/CW-12/19/20 በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፣
የግዥዉ መጠን ከብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 08 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ( ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት የዋጋዉን አንድ/1/ በመቶ በጨረታ ሰነዱ መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ( ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በባህር ዳር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በግዥና ፋይናንስ ቡድን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ10/09/2012 ዓ/ም እስከ 24/09/2012 ዓ. ም 11 ፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ11 ፡30 ወዲያዉኑ ይታሸጋል፡፡
ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግዥና ፋይናንስ ቡድን በቢሮ ቁጥር 8 በ25/09/2012 ዓ/ ም በ3 ፡30 ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 16 93 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስ/ ከተማ ል ማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ


Posted: በኩር ግንቦት 10ቀን 2012

Deadline: June 1, 2020


© walia tender

Report Page