Cater oromia marem1

Cater oromia marem1

Walia Tender

                  የጨረታ ማስታወቂያ

መ/ቤታችን በስሩ ለሚያስተዳድራቸው የዞን እና ወረዳ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙት የሕግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት ሐምሌ 1/2012 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓም ለ6(ስድስት) ወር ለሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ማንኛውም በጨረታው ስመካፈል የሚፈልግ ደርጅት ወይም ግለሰብ፡

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ቢሮ ወይንም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው 2012 የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተመዘገቡ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ
የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00( ሰላሳ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዞኑ እና ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤቶች በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የዋጋ ማቅራቢያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞንና በወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤቶች ለዚሁ የተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
ተጫራቶች ጨረታ ማስከበሪያውን ከመቶ ሁለት (2 ፐርሰንት) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (C P O) እና የ የምግብ እህል ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 በተከታታይ ቀን በዓየር ላይ ውሎ በ16 ቀን ከረፋዱ በ4 ፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት በ4 ፡30 ሰዓት በዞን እና በወረዳ ማረሚያ ቤቶች አስ/ ጽ/ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎችና የመ/ ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
የዞኑ ወይንም የወረዳ ማረሚያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብ የሚችል
ማረሚያ ቤቶች የሚገኙበት ከተሞች


ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114-66-53-94/091190658 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 28 ቀን 2012

Deadline: June 20, 2020


© walia tender

Report Page