Cater oromia 2..

Cater oromia 2..


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 26/2012

አልሚ ምግብ (FAMIX) ለመግዛት ለ2 ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በተለያዩ የክልሉ ዞኖች ውስጥ ለሚገኙና የምግብ እጥረት ላጋጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለተጨማሪ የምግብ አገልግሎት የሚውል 5400 (አምስት ሺህ አራት መቶ) ኩንታል አልሚ ምግብ (FAMIX) ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፣

ለዘመኑ የታደሰ የሥራ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
የግብር ግዴታ ለመወጣታቸው ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
ተጫራች ድርጅቶች ጊዜ ያላለፈበት ISO የምዝገባ የምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራች ድርጅት የአልሚ ምግብ/ፋሜክሱን በተጠየቀው ደረጃና ጥራት ለማምረት የሚያስችል የማምረቻ ፋብሪካ ያላቸው መሆን አለባቸው ፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::
የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (Tax payer Registration cetificate)ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
ተጫራች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
ተጫራቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ) በመክፈል ከኮሚሽኑ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 20 መዉሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዳቸውን ዋናና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግና የተጫራች ስም፣ፊርማ፣ማህተምና ሙሉ አድራሻ በመግለጽ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 21 ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች ያልተገደበ የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና Unconditional Bid Bond / የጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ CPO ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ በቅድሚያ ያስይዛል፡፡
ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን በ 4:00 ተዘግቶ በ4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁ.21 ውስጥ ይከፈታል፡፡ የጨረታው የመክፈቻ ቀን ፣ በዓል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተባለው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው Specification / መሠረት ነው፡፡
አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈርሙ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና 10% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
የጨረታው የመወዳደሪያ ሃሳብ አሸናፊው ድርጅት ከኮሚሽኑ ጋር ውል ከተገባበት ቀን ጀምሮ ለ 45 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የአንዱን ኩንታል ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ መግለጽ አለበት፡፡
ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ተገልጾላቸው ውሉን ከፈረሙበት ዕለት ጀምሮ ምርቱን በተጠየቁ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011888909 መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ ሣሪስ አዲስ ጐማ ፊት ስፌት የኦሮሚያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ፊንፊኔ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 15 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page