Cater kilinto7

Cater kilinto7


ማስታወቂያ የጨረታ

በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ለቀጠሮ ለህግ እስረኞች ለምግብ አገልግሎት የሚውሉ

በጥሬው የተከካ አተር ክክ፣ በጥሬው የተከካ ባቄላ ክከ፣ የተቆላ አተር ከክ፣ የተቆላ ባቄላ ክክ፣ ምስር ክክ፣ ጨው፣ ተቀንጥሶ የተዘጋጀ ዛላ በርበሬ፣ቀይ ሽንኩርት፣ጥሬ ጎመን ዘር፣ የዳቦ እርሾ፣የዳቦ ማኮፈሻ፣ካሮት፣ድንች፣ጥቅል ጎመን፣የሻይ ቅመም፣ቅርንፉድ፣ጦስኝ፣ ኮረሪማ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ቃሪያ፣ሻይ ቅጠል፣ነጭ ሽንኩርት፣ዕርድ፣ደረቅ ዝንጅብል የተላጠ፣ነጭ አዝሙድ፣ጥሬ አብሽ፣ቲማቲም ድልህ፣ለጋ የምግብ ቅቤ፣ከኖር፣ጥምዝ፣ከሙን፣ቆንዶ በርበሬ፣ በሶብላ እና
የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር በውልተዋውሎ መግዛትይፈልጋል::
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡
የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፡፡
የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣የታደሰ የዘመኑን ንግድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
የመንግሥት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም::
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቀጠሮ ማረ/ቤት አስተዳደር ገንዘቡን ገቢ በማድረግ ከባንክ በተመሰ ከረለት ሲፒኦ 50,000.00 ማስያዝ ይኖ ርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን / ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረስ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
ማንኛውም ተጫራቶች የሚያስገቡት ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና ስሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ ፣በፍለድ የጠፋ ሰነድ ፣ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው ማቅረብ አለባቸው::
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይ መለስ ብር 50.00 / ሃምሣ ብር/ የኢትዮጵያ ንግድ ባ ንክ በቀጠሮ ማረፊያ ቤቶች አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ::
ጨረታው በ2/11/2012 ዓም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን በመስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች እስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ::
አድራሻ:- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖስጂ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ :-011 47163 33/ 0114718986

የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር

/ ቂሊንጦ/



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012

Deadline: June 9, 2020


© walia tender

Report Page