Cater boru meda hospital4
የበሰለ ምግብ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ለ COVD -19 (ኮሮና ቫይረስ) ታካሚዎችና ለጤና ባለሙያዎች የሚውል የበሰለ ምግብ በመጫረቻ ሰነድ የቀረቡትን ዝርዝሮች በጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት መያዝ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት፡
1.1. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለሁሉም ሎት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ( የሥራ ፈቃድ) ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
1.2. የተጨማሪ እሴት ታክስ | ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ
1.3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tm) ተመዝጋቢ የሆኑ
1.4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመቶ ብር(100.00) ዘወትር በሥራ ሰዓት በሆስፒታል ግቢ በመቅረብ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀን (አስራ አምስት) ቀን ውስጥ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
1.5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ዋናው እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4 ፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚያው ዕለትም 4 ፡30 ፤ ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መጫረቻ ሰነድ ላይ ሲሞሉ ለሁሉም ሎት ቫትን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል። የውለታ ማስከበሪያ በመመረያው መሰረት ውል ይወስዳሉ፡፡
1.6. ተጫራቶች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000.00 ( አራት ሺህ ) ብር ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ምግብ የሚያቀርቡትና የሚዘጋጀውም ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ መሆን ይኖርበታል፡፡
1.7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ በቀረበው የጨረታ መመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
1.8. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቶች በሚከፈትበት ቀን ቢኖሩም ባይኖሩም ከመከፈት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም፡፡
1.9. የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይንም በበዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033 2415005 ደውለው ይጠይቁን።
የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል
Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012
Deadline: June 13, 2020
© walia tender