Cater arbaninch pr3

Cater arbaninch pr3


የጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ማረሚያ ተቋም በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች መኖ እህል በግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማሳወጅ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ በበጀት ዓመቱ የታደሰ
የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት /TIN/
ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዚጋቢ
የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወርቀት
ሌሎች ይጠቅሙኛል የሚላቸዉን መረጃዎች አያይዞ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ከላይ በተገለጸዉ ዝርዝር መሠረት፡፡

የጨረታ ማስከበ ሪያ ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ/አርባ ምንጭ ማረሚያ ተቋም ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
የጨረታዉን ዝርዝር የሚገልጽ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመከፈ ል አርባ ምንጭ ማረሚያ ተቋም ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማንኛዉም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በፖስታ የታሸገ ኦርጂናልና ኮፒ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የመንግሥት የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመግዛት ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን፡፡
ጨረታዉ ሣጥን በ16 ኛ ቀን 4 ፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚህ ቀን 5 ፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡
የጨረታዉ መከፈቻ በበዓላት ፤ቅዳሜና ዕሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
የጨረታ አሸናፊ የሆነ ያሽነፋቸዉን ዕቃዎች ማሸነፋቸዉ ሲረጋገጥላቸዉ ቀረበዉ ዉል በመግባት በራሱ ወጪ እስከ ማረሚያ ተቋሙ ግቢ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡

ማሳሰቢያ፡-

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የተጫራቾች መገኘት አለመገኘት የጨረታዉን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

ተጫራቹ ለሚጫረታቸዉ ዘርፎች በግዥ ሠነዱ ላይ በተገለጸዉ መሠረት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
ሁሉም በማስታወቂያ ላይ የተገለጹ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥ ር፡- 046 881 0093/046 881 0049 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በደቡብ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መንግሥት የአርባ ምንጭ ማረሚያ ተቋም



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: June 13, 2020


© walia tender

Report Page