Car used buna bank1

Car used buna bank1

ADMIN3 (Selamawit)

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ. ማ

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር፤ ቡኢባ/ ሕአዳ/ ሐራጅ/012/2012



ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

የሐራጅ ደንቦች፣

ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4 ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ( ሲ. ፒ. ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ:: አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል አለበት:: ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው::
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ዋና መ/ቤት አፍሪካ ጎዳና ሩዋንዳ መታጠፊያ በሚገኘው ሕንፃ 5ኛ ፎቅ በሚገኘው የጨረታ አዳራሽ ነው::
የተጫራቾች ምዝገባ ከአያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::
ገዢ ተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የስም ማዛወሪያ ክፍያ፤ ዓመታዊ የቦሉ ክፍያና እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል::

ተሽከርካሪዎቹ ቀረጥ ያልተከፈለባቸው ሲሆን፤ ገዢ ከቀረጥ ነፃ መብት ያለው መሆን ይኖርበታል፤ ካልሆነ ደግሞ ቀረጡን እና ተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል የሚጠበቅበት ይሆናል::

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለሐራጅ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት አበዳሪ ቅርንጫፍ ወይም ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለመጎብኘት ይችላሉ::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-229-10-44 ( እህል በረንዳ ቅርንጫፍ) ፣ በ011-158-08-24/25 ( ዓብይ ቅርንጫፍ) ወይም በስልክ ቁጥር 011-1-58-08-63/ 0111-26-36-09 ( ሕገ ኣገልግሎት ዳይሬክቶሬት) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::


Posted: ሪፖርተር ግንቦት 23 ቀን 2012

Deadline: July 19, 2020


© walia tender

Report Page