Car elet derash transport

Car elet derash transport


ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ግዥ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት በ2012 በጀት ዓመት 40 (አርባ) ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች ከነተሳቢያቸው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
በተለያዩ ድርጅቶች በተሽከርካሪና ተሳቢ አቅርቦት ላይ መሰማራታቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ/ጀምሮ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመ ለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል አቃ ቂ ቃሊቲ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ሂ/ደ/የስ/ሂ/ዳይሬክቶሬት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፣
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም Bid Bond Guarantee ጠቅላላ የሚጫረቱበት ዋጋ 2% በማስያዝ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፣
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ ታክስ የሚያካትት መሆኑንና አለመሆኑን በግልጽ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ከመመሪያው ጋር አባሪ ሆኖ የተዘጋጀውን ቴክኒካል መገምገሚያ በጥንቃቄ በመገንዘብ የቴክኒካል ሰነድ እና የፋይናንሽያል ሰነዶቻቸውን በኦርጅናልና በፎቶ ኮፒ ለይተው በተለያየ ፖስታ በማድረግ፣ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ ከ70/100 እና የፋይናንሻል ሰነድ ከ30/100 የሚገመገም መሆኑን አውቀው ለየብቻ አዘጋጅተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የቴክኒካል ግምገማ ውጤት 70/100 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለፋይናንሻል ውድድር/ግምገማ ያልፋሉ፡፡ በቴክኒካልና ፋይናንሻል አጠቃላይ ድምር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል።

ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለምን ያህል ጊዜ ፀንቶ እንደሚቆይ በጨረታ ሠነዱ ላይ መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
በጨረታ ሠነዱ የሚጠቀሱ ዋጋዎች በሙሉ በብር/በኢትዮጵያ ሕጋዊ ገንዘብ መሆን ይኖርበታል፡፡
የጨረታ ማቅረቢያ ሠነዶች በሙሉ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተፅፈው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ. ም ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ዕለት ከቀኑ በ8 ፡30 ተጫራቾች ወይ ም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

የጨረታ አሸናፊ ውጤት እንደተገለፀለት በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ/የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና ጠቅላላ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በማስያዝ ውል ይፈፅማል፣

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0114390075/1569/3592/0114391027

ፋክስ 0114-39-63-36 ፖሳቁ. 2562 አዲስ አበባ መጠየቅ ይችላሉ

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፊት ለፊት አሁን ትሬን ባትሪ መሸጫ ሕንፃ በስተጀርባ

70 ሜትር ገባ ብሎ ነው

የዕለት ደራሽ የዕርዳታ ትራንስፖርት ድርጅት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: July 1, 2020


© walia tender

Report Page