Car eawc1

Car eawc1

Walia Tender

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

ሀ) ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እቃዎቹ በሚገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ በተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ እና በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለትም ጊቤ፣ (ሀዋሳ (ሻሎ)፣ አሰላ ጎንዴ ፣ ቡሬ (አንገር ጉትን)፣ ባህርዳር (ቁንገላ)፣ ቻግኒ፣ አርዳይታ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 150.00( አንድ መቶ ሃምሳ ብር ) በመክፈል ስተራ ፊደል ለተገለፁት ቦታ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

ለ) የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሔደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዘርፉ ጽ/ቤት እና ጊቤ፣ (በሀዋሳ፣ በአሰላ፣ በቡሬ፣ በባህርዳር፣ በቻግኒ፣ በአርዳይታ እና ሞጆ) ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ክፍት ይሆናል፡፡

ጨረታውም በ10 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 10 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ የቅ/ ጽ/ ቤት ሰነዶች ተሰብስበው ከመጡ በኋላ በ13 ኛው የስራ ቀን፡

ሎት 2. ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት
ሎት 3 ከጠዋቱ 6 ፡00 ሰዓት
ሎት 4 እና 5 ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ጸ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አዲስ አበባ ይከፈታል፡፡

ሐ) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም:

ሎት 2 ፡- ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ ብር 10,000.00 ( አስር ሺህ ብር )
ሎት 3 ፡- ለከባድ ተሽከርካሪዎችና ተሳቢዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ ዋጋ ብር 15,000.00 ( አስራ አምስት ሺህ ብር)
ሎት 4 ፡- ለእርሻእና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት መሳሪያ ብር 15,000.00 ( አስራ አምስት ሺህ ብር)
ሎት 5 ፡- ለተለያዩ የተሽከርካሪ፣የእርሻና የኮንስትራክሽን መሳሪያ ሞተሮች( ኢንጅኖች) እና ኮምፖነንቶች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት
ሎት 5.1 የተለያዩ ኮምፖነንቶች የመግዥያ ዋጋውን ብር 2% እና
ሎት 5.2 ለየተለያዩ ሞተሮች ብር 500 ( አምስት መቶ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ( የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ) ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
መ) ተጫራቶች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ በፊት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመላከት ማቅረብ አለባቸው፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቃሊቲ ጉምሩክ የባቡር የመጨረሻው ጣቢያ ፊት ለፊት ከአዋሽ ባንክ ጀርባ

ስልክ ቁጥር 0114-43-20-18/0114-70-84-70

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን


የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 30 ቀን 2012

Deadline: June 19, 2020


©walia tender


Report Page