Car chemical indus20..

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሙሲፋ /11/2012
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የተለያዩ ተሽከርካሪ መኪና በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 ከቫት በፊት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ጠመንጃ ያዥ አጠገብ የሚገኘውን ጋራድ ሞል ሦስተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ:: ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO ወይም ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ. ም. ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ከላይ በተጠቀሰው ሲሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ. ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት በአቅርቦት አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል ። ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን
ስልክ ቁጥር፡- 0114420216
ፋክስ፡-0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዲስትሪ
ኮርፖሬሽን የሙገር
ሲሚንቶ ፋብሪካ
Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 08 ቀን 2012
Deadline: June 12, 2020
© walia tender