CSA
#CentralStatisticsAgency
የመስከረም ወር 2014 ዓ/ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 34.8 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ወርሃዊ ሪፖርት አመላከተ።
የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በማነፃፀር የሚገኘው ውጤት ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት ሁኔታን የሚያሳይ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የምግብ ዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 42.0 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
በተለይ በዳቦና እህሎች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በያዝነው ወርም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፦
- የሩዝ፣
- የእንጀራ፤
- የዳቦ፤
- የጤፍ፤
- የስንዴ፤
- የማሽላ፤
- የበቆሎ፣
- የገብስ፣
- የስንዴ ዱቄት፣
- የፓስታና ማካሮኒ ዋጋ በፍጥነት ጨምሯል፡፡
በተጨማሪም ፦
- ሥጋ፣
- የምግብ ዘይት (ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር ከውጭ የሚገባው የምግብ ዘይት ዋጋ እጥፍ በለይ ሆኗል)፣
- ወተት፤
- አይብና ዕንቁላል፤
- ቅቤ፣
- ቅመማ ቅመም (በዋናነት ጨውና በርበሬ)
- ቡና የዋጋ ጭማሪ በዚህም ወር በመቀጠላቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ በፍጥነት መጨመር አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወር ከፍ ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ25.2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
ከምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም ፦
- በአልኮልና ትምባሆ ፣
- ልብስና ጫማ፣
- አነቃቂዎች (ጫት)፣
- የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል)፣
- የቤት መስሪያ እቃዎች
- የቤት ኪራይ፣
- ሲሚንቶ የቤት ኪዳን ቆርቆሮ ፣
- የቤት ዕቃዎችና የቤት ማሰገጫዎች፣ ህክምና እና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው፡፡
አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በ4.0 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
Credit : Capital Newspaper
@tikvahethiopia