COVID-19 UPDATE

COVID-19 UPDATE

ኤልሻዳይ




በኢትዮጵያ ተጨማሪ ዘጠኝ (9) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!


በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 442 ሰዎች መካከል ዘጠኙ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንንም ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 65 ከፍ ብሏል።


የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ዛሬ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሁሉም ግለሰቦች የጉዞ ታሪክ አላቸው።


ከግለሰቦቹ መካከል ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ አንድ ኤርትራዊ ቀሪዋ ደግሞ የህንድ ዜግነት ያላት ናት።


አራቱ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።


ሁለቱ የቱርክ፤ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ የእንግሊዝ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን፤ ሁሉም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲያደርጉ መቆየታቸውን አውስተዋል።


የ20 ዓመቷ ህንዳዊት የአሜሪካ እንዲሁም የ40 ዓመቱ ኤርትራዊ ደግሞ የዱባይ ጉዞ ታሪክ ያላት ናቸው።


በጽኑ ህሙማን ክፍል ከሚገኙት ሁለት ግለሰቦች መካከል አንዱ የጤና መሻሻል በማሳየቱ ከክፍሉ መውጣቱንም ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።


እስካሁን ባለው ሂደትም በኢትዮጵያ ለሶስት ሺህ 232 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን ጠቁመው፤ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 57ቱ የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።


አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።



የታማሚዎች ሁኔታ ፦


ታማሚ 1 - የ20 ዓመት ህንዳዊት ከአሜሪካ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለች።


ታማሚ 2 - የ37 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከቱርክ የመጣና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።


ታማሚ 3 - የ38 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከቱርክ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ።


ታማሚ 4 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ያለች።


ታማሚ 5 - የ46 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ።


ታማሚ 6 - የ33 ዓመት ኢትዮጵያዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ።


ታማሚ 7 - የ29 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከዱባይ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ያለች።


ታማሚ 8 - የ39 ዓመት ኢትዮጵያዊት ከUK የመጣችና በለይቶ ማቆያ ያለች።


ታማሚ 9 - የ40 ዓመት ኤርትራዊ ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ ያለ።




በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦


• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,232

• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 442

• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 9

• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ያሉ - 57

• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1

• ያገገሙ - 4

• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 2

• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2

• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 65



Report Page