CHEENA

CHEENA


"...ከአንድ ቤተሰብ 5 እና 6 ሰዎች የሞቱ አሉ" የጭና ነዋሪዶች 

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ "ጭና" የህወሓት ታጣቂዎች ከአንድ መቶ በላይ ንፁሃንን መግደላቸውን ነዋሪዎች አሳውቀዋል።

ግድያው የተፈጸመው አካባቢው በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ ሲሆን ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ህጻናት በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።

አንድ የጭና አጎራባች ቀበሌ አብጥራ፣ ነዋሪ የሆኑ አስማረ ታፈረ የተባሉ ግለሰብ ለቢቢሲ በሱጡህ ቃል ፥ ነሐሴ 12/2013 ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በአካባቢው የህወሓት ታጣቂዎች በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና ውጊያ መካሄዱን ጠቁመዋል።

ጦርነቱ እስከ ነሐሴ 29/2013 ዓ.ም ድረስ መካሄዱን የገለፁ ሲሆን ፥ እስካሁን ድረስ ተገድለው የተገኙ 119 ሰዎች በጦርነቱ ያልተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው ብለዋል።

"ይህ ቁጥር መሞታቸው ታውቆ ለቅሶ እየተለቀሰ ያለ ነው" በማለት ይህ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪው ተናግረዋል።

እንደነዋሪው ገለፃ ፥ ከአንድ ቤተሰብ አምስት እና ስድስት ሰዎች ሞተዋል።

ሌሎች የአይን እማኝ ነን ያሉ ነዋሪዎች በጭና ተክለሃይማኖት ቀበሌ የተገደሉ ንፁሃ ከ200 በላይ መሆናቸውን ዛሬ አመልክተዋል። 193 የሚሆኑት በጭና ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን መቀበራቸውን አመልክተዋል።

ከ20 በላይ የሚሆኑት በዲያ ጊዮርጊስ መቀበራቸውን አሳውቀዋል።

አሁንም ተጨማሪ አስከሬን እየተገኘ መሆኑ የተመላከተ ሲሆ የደረሱበት ያልታወቀ እንዳሉም ነው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ከ15 ሺ በላይ የቀበሌው ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል ተብሏል። 

የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ፣ በጭና ቀበሌ ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር ለ11 ተከታታይ ቀናት ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር ተናግረው፤ ታጣቂዎቹ "እንስሳትን እና የአርሶ አደር ንብረቶችን መዝረፍ . . .እንዲሁም ማበላሸት" መፈጸማቸውን አመልክተዋል።

አቶ ሰውነት ፤ በዚህ ሳምንት በአካባቢው ላይ በተደረገ ቅኝት የበርካታ ንፁሃን የአካባቢው ነዋሪዎች የጅምላ መቃብር መገኘቱን አመልክተዋል።

ከአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም ከተገኙ የጅምላ ማረጋገጥ እንደተቻለው እስካሁን 119 ሰዎች መገደላቸው መታወቁን ሪፖርት አድርገዋል።

የወረዳ አስተዳዳሪው ፤ ዛፍ ጋር ታስረው የተረሸኑ ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ ህጻናት እና ከቅዳሴ እየተመለሱ የነበሩ ቀሳውስት ጭምር መኖራቸውን ተናግረዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው፥ "በቀላሉ ሊያሳልፋቸው ያልቻለ ሕዝብ በመሆኑ፤ ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ ነው" ያሉ ሲሆን ፤ የህወሓት ታጣቂዎቹ አባሎቻቸው ሲማረኩ እንዲሁም ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው "በብስጭት" ጭና ቀበሌ ላይ በንጹሃንና በጦርነቱ ተሳታፊ ባልሆኑ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ አካሂደዋል ብለዋል።

#Reuters #BBC #FBC

@tikvahethiopia

Report Page