Build1 amh

Build1 amh


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አሕሥኮድ 57/2012

የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ባለ 750 ሊትር ሚክሰር፣ ባለ 350 ሊትር ሚክሰር፣ ቶታል ስቴሽን እና መገናኛ ሬዲዮ ህጋዊና ብቃት ያላቸውን ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ድርጅቱ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

1በዘርፉ የተሰማሩና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣

2የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ፣

3 የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ኣያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 / ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ባህር ዳር ከተማ አማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 11 ወይም አዲስ አበባ አራት ኪሎ የብአዴን ህንጻ የአህስኮድ የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ (ስልክ +251111265652)ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሙግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ( ቢድ ቦንድ) ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2% ከዚህ በታች በተመለከተው ሰንጠረዥ መሠረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ(CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( Unconditonal Bank Guarantee) Amhara Building Works Construction Enterprise በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡ ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡

8.ተጫራቾች የቴክኒክ እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አንድ ቴክኒካል እና አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና ኣንድ ቅጅ ፋይናንሻል ማቅረብ አለባቸው፡፡

9.የጨረታ ሰነዱን በአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የማ/ተሸ/ግዥና አቅ/ ኬዝ ቲም ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር ) ከቀኑ 8 ፡ 00 ሠዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 15 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8 ፡ 00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የማሽ/ተሽ/ግዥና አቅ/ኬዝ ቲም ቢሮ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15 ኛው ቀን ከቀኑ 8 ፡ 00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 8 ፡ 30 ይከፈታል፡፡ 15 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8 ፡ 00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 8 ፡ 30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ውድድሩ በዚሁ ዕለት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

11.የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን እቃዎች አህስኮድ ዋና ቢሮ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡

12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058320-40 01 መላክ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0918784490/058-320-51 85/0918784490 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት


Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 07 ቀን 2012
Deadline: May 29, 2020


© walia tender

Report Page