Build sale other9

Build sale other9


አገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር NCB AWWCE 09/ 2012

የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የክልሉን የውሃ ሀብት በማልማትና ለንፁህ መጠጥ ውሃና ለዘመናዊ መስኖ አገልግሎት በማዋል የክልሉን ብሉም የአገሪቱን እድገት ለማፋጠን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ለድርጅቱ ለመጠጥ ውሃ እና ለመስኖ ዝርጋታ አገልግሎት የሚውሉ

ሎት አንድ ጀነሬተር፣
ሎት ሁለት ሰብመርሰብል ፓምፕ እና
ሎት ሶስት ሰርፌስ ፓምፕ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ከሆኑ ተጫራቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሆነ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1- 3 የተጠቀሱና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ፣ የተጫራቾች መመሪያ፣የቴክኒክ መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር) በመክፈል አማ ራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ከድርጅቱ ዋና ግቢ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 32 መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም ለጀነሬተር፣ለሰብመርሰብል ፓምፕና ለሰርፌስ ፓምፕ በተናጠል ብ ር 150,000 ( አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር) በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ለ120 ቀናት እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን ጠቅሰው በታሸገ ፖስታ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል ከሚያሳይ ብሮሽር ጋር ለየብቻ በማሸግ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 33 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20 ኛ ቀን ከቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት በ8 ፡30 የሚከፈት ይሆ ናል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከናወናል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናትና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን በመረዳት የጨረታ ዋጋ በውል ዘመኑ በሙሉ የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች የማቅረቢያ ጊዜ ቅድሚያ ክፍያ ከተከፈለው ቀን ጀምሮ የሚታሰብ በ90 ቀናት ውስጥ ይሆናል ኤልሲ(C) ወይም ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንደመስፈርት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፡፡አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በደብዳቤ በተገለፀለት በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ ማቅረብ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡ይህ ካልሆነ ግን የውል ማስከበሪያው የሚወረስ ይሆናል፡፡ክፍያን በተመለከተ ደግሞ 30% ቅድሚያ እና 70% ደግሞ እቃዎችን ካስረከበ በኋላ የሚከፈል ይሆናል፡፡
ማንኛውም ተጫራቾች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከድርጅቱ ዋና ግቢ ግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
የፋይናንሻል ጨረታው መክፈቻ ቀን በቴክኒካል ለተመረጡ ብቻ በደብዳቤ ይገለፃል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለገ በድርጅ ቱ ዋና መ/ ቤት ቢሮ ግዥ/ የስ/ ሂደት 3 ኛ ፎቅ ቁጥር 33 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር፡- 058-222-14-79 ቀበሌ 14 አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ባህር ዳር



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 05 ቀን 2012
Deadline: June 1, 2020


© walia tender

Report Page