Buil lab chm sale dese tisu30

Buil lab chm sale dese tisu30


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል ቀጥሎ ያሉትን እቃዎች

የቧንቧና ኮንስትራክሽን እቃዎች
ኬሚካሎችና የላብራቶሪ ቁሳቁሶች
ፕላስቲክ የግብርና ግብአቶች እና
ኤሌክትሮኒክስ ማቅረብ የሚችሉ ነጋዴዎችን በየስራ ዘርፉ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡

በዘርፉ እና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፤
የግዥው መጠን ብር 50,000.00 ብር /ሃምሣ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙ እቃ ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ/ እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 1% / አንድ ፐርሰንት/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሠነድ ከደሴ ቲሹ ካልቸር ማእከል በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 / ሃምሣ ብር ብቻ/ ከፍሎ መውሰድ ይችላል፡፡
ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ኛው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው በኤንቨሎፕ ላይ ስማቸውንና ስልክ ቁጥር በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
በጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ ቢሮ በ16 ኛው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ታሽጐ 4 ፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጐ 4 ፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ውድድሩን በሎት ወይም በተናጠል ሁለቱንም አማራጭ የመጠቀም መብቱ መ/ቤቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨታው መረጃ ከፈለጉ ማዕከሉ ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር፡0338997519/0910704256/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ደሴ ቲሹ ካልቸር ማዕከል



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 11 ቀን 2012
Deadline: June 3, 2020


© walia tender

Report Page