Buil hulet eju 2

Buil hulet eju 2


Eid Mubarak!

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሁ/እ/እ/ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ወረዳው እያስገነባው ላለው የተለያዩ ቢሮዎች

የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ፤
የፊኒሽግ ማቴሪያል /finishing material/፣
ሲሚንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛሉ፡፡

በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
የግዢው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር) ከሁ/ እ/እ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከረዳት ገ/ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጥ ቅል ዋጋ 1% (1/100) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ለሚያዝ ገንዘብ በሁ/እ/እ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተገለፀበት ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት የዕቃ/አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10% የተሽከርካሪ ኮንትራት ጥገና ከሆነ 3% የግዥ ውል ማስከበሪያ ፕሮፎርማንስ ቦንድ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዘዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconcitional bank grantee/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የዕቃውን ግዥ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሁ/እ/እ/ወ/ገ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16 ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡ (የተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ኮፒ ማስገባት ለመ/ቤቱ ደህንነት እንጂ ጨረታ መወዳደሪያ መስፈርት አያገለግልም)
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 6 የጨረታ ጋዜጣው በወጣ በ 16 ኛው ቀን 3 ፡30 ሰዓት ታሽጐ በ4 ፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን መክፈት መብት አለው፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
ውድድሩ በድምር /በሎት ስለሆነ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁ ዝርዝሮችን በሙሉ መሙላት አለባቸው ::
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0586610005 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡
መ/ቤቱ የሚገዛውን ወይም የሚያሰራውን ሥራ ዕቃ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አሸናፊው ተጫራች ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ መ/ቤቱ ከሚፈልግበት ቦታ ድረስ ሊያቀርብ የሚችል መሆን አለበት ::
በተጨማሪ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 14 ቀን 2012

Deadline: June 6, 2020


© walia tender

Report Page