Buil con AARC 122

Buil con AARC 122


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አስከመባ/ ግብዓት/ ቡ2/016-2/2012

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ለተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል ሰብ ቤዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡

ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተቆፋሪ ውጤቶችና ዕቃዎች አቅራቢነት እና ሌሎች በዘርፉ አግባብነት ያላቸው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይንም ድረ ገፅ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 132 መግዛት ይችላሉ፡፡
ማንኛውምተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond/ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ በባለ ሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻስ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስልክ ቁጥር፡-011-3-72-28-15/011-3-72-28-25

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 16 ቀን 2012

Deadline: June 5, 2020


© walia tender

Report Page