Buil addisvro1

Buil addisvro1


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር እእከመባ/ግብዓት/ቡ-/013-2/2012 የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2012 በጀት አመት ለመንገድ ግንባታ ግብዓት የሚሆን ኮንክሪት ቱቦ ባለ 1000 ሚ.ሜ በድጋሚ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ:

ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታከስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ድረ-ገፅ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማ ይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ።
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ certified payment order (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional Bank Guarantee/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ስሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል። መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011-3-71-41-03/011-3-72-28-15

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 14 ቀን 2012

Deadline: June 5, 2020


© walia tender


Report Page