Bui EEP 30

Bui EEP 30


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEP/PP/NCB/14/2012

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ብዛት ያለው የፒፒሲ ስሚንቶ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳ ደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት እና ሰዓታት ሜክሲኮ ወደ ቄራ መውረጃ አዲሱ ኬ ኬር ሴንተር አንደኛ ፎቅ ከሚገኘው ዋናው መ/ቤት ፕሮኪዩርመንት ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 / ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተውን የፒፒሲ ስሚንቶ ዋጋ ዝርዝር እና ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEPPP/NCB/14/2012 የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች ሙሉ ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፤ ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት
ከፈለጉ ደግሞ በስልክ ቁጥር፡- 0115581522/011-5 58 07 81 መደ ወል ይችላሉ፡፡



የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 18 ቀን 2012
Deadline: June 10, 2020


© walia tender

Report Page