Bui AWWC133

Bui AWWC133


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 59/2012
የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት በዳንግላ የገጠር ሽግግር ማዕከል በቻግኒ የገጠር ሽግግር ማዕከል በቡሬ ላንድ እስኬፒንግ ለሚገነባቸው ልዩ ልዩ ግንባታዎች ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ SHS, RHS እና CHs ብረቶችን ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣ የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ አማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 16 የማይመለስ ብር 200.00 ( ሁለት መቶ ብር ) በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ። የጨረታው ውድድር በሎት (በምድብ) ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት (ምድብ) ለተጠየቁ እቃዎች ለሁሉም ዋጋ መሞላት አለበት። ነገር ግን ውል ሰጪ (ገዥ) ድርጅትን ጠቃሚ ሆኖ ከተገኜ የተወዳዳሪዎችን ዋጋ በማየት በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ድርጅት ሊመረጥ ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 15 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8 ፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8 ፡30 ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል።
በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ መሟላት ያለበት፡

3.1 በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ፣
3.2 ማንኛውም የወቅቱን የመንግሥት ግብር ለመከፈሉ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ፣
3.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
3.4 የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በ ተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል። ነገር ግን የሚያሲይዘው ማስከበሪያ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) መብለጥ የለበትም።
3.5 ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ከመረከቡ በፊት ናሙና እስቀርቦ የዕቃዎችን ትከከለኛነት የጥራት ቴስት በማሰራት እና በድርጅቱ አማካሪዎች በማረጋገጥ ትከከለኛነቱን ሊያሟላ ብቻ ይረከባል። ከህጋዊ ተቋማት ለሚደረግ የጥራት ማረጋገጫ ከፍያ በሻጭ ይሸፈናል።
3.6 በጨረታ ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ3 የሥራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
4 በጨረታ ውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት እቃዎቹን በራሱ ወጪ ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት ከተማ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ ያስረክባል፡፡

5. የጨረታአሸናፊውለአሸነፉበትጠቅላላ ዋጋቫትን ጨምሮ 10% የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና (የውል ማስከበሪያ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል።

6 የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

7. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችሉም።

8. በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡

9. ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከገዛው ዕቃ መጠን ላይ በየሎቱ ጠቅላላ እቃ አይነትና መጠን ወይም በእያንዳንዱ የእቃ አይነትና መጠን ለገዥ ጠቃሚነው ብሎ ከታመነ ውል ሲይዝ 50% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል። ከውለታ በኋላ ሊጨምር 50% ይችላል፡፡

10. ከጨረታ ሣጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።

11. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ውለታ ወስዶ ናሙና ለአማካሪ በማቅረብ ሲፀድቅለት ብቻ ያቀርባል፡፡

12. ውድድሩ በሎት ድምር አሸናፊ የሚል ቢሆንም ገዥ ድርጅቱን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊውን ሊመረጥ ይችላል፡፡

13 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 218 07 11/ 0918 71 68 23/09

የአማራ የሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 16 ቀን 2012

Deadline: June 8, 2020


@ walia tender

Report Page