Bui AARA21

Bui AARA21


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢው መለያ ቁጥር ፡- አስከመባ/ ግብዓት/ ቡ-1/020/2012

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከታች የተጠቀሰው ኮንክሪት ሚክስ C-25 እና C-30 በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል ::

ስለዚህ:-

ተጫራቾች በዘርፉ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ከሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ መመዝገብ ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ ኮንክሪት ለማምረት የሚያስችል ፍቃድ ካለው ግለሰብ ማህበር የተሰጠ ህጋዊ /በፌዴራል የሰነዶች ማረጋገጫ ፅ/ቤት የተረጋገጠ /ውክልና እና የኮንክሪት ማምረቻ ማሽኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡

ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመ ክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ጊዜ ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሠንጠረዥ በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡ ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡


ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ፡- ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ

ስልክ ቁጥር፡- 011-3-72-28-15/011-3 71-41-03/ 011-8-72-00-47

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 21 ቀን 2012

Deadline: June 16, 2020


© walia tender

Report Page