Bui 1

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE ፕሮ/11-10B/41/2012
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለመከላከያ ዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ለተካተተው አዲስ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተያያዥ ሥራዎች የሚያስፈልግ የ Galvanized Steel Pipe ግዥ ለመፈፀም በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስ ለ ሆነም:
ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ/ በመክፈል ቅዳሜን ጨምሮ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ጦር ሀይሎች ፊት ለፊት በምድር ሀይል ግቢ ውስጥ ባለው ቢሮአችን ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ::
የጨረታ አሽናፊው ወደ ስራው ሲገቡ የውለታው 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ግንቦት 19 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 5 ፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
ጨረታው ግንቦት 19/2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 5 ፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
ፕሮጀክቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ምድር ኃይል ግቢ ውስጥ በሚሰራው ህንፃ ፕሮጀክት መምጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
ለበለጠ መረጃ :- በስልክ ቁጥር 0118-49 38 23 ይደውሉ ::
Posted: ሪፖርተር ግንቦት 02 ቀን 2012
Deadline: May 27, 2020
© walia tender