Bu AAWSA1

Bu AAWSA1

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር NCB/GOV/G005/2012

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን 14,500 ሜትር ኪዩብ የገረጋንቲ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉይጋብዛል።

ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት መገናኛ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ምድር ቢሮ ቁጥር 113 በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
ማንኛውም ተጫራች በመንግስት የግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ-ገፅ የተመዘገበ፣ ለዘመኑ ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ በመወዳደሪያ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
ጨረታውን ለመሳተፍ ብር 25,000.00 / ሃያ አምስት ሺ ብር / የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብማስያዝ ይኖርበታል።ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሠነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀውሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለ60/ስልሳ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል ።
የጨረታ ሠነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
ጨረታው ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ . ም . ከሰዓት 8 ፡ 00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከሰዓት በ 8 ፡ 30 ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም።
የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡
ገዥው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን ዕቃዎች በ20% የመጨመር ወይም በ20% የመቀነስ መብቱ፡ የተጠበቀ ነው።
የባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- መገናኛ ከሚገኘው በተለምዶ 24 ቀበሌ የገቢዎች ሚኒስቴር አጠገብ ያለው ሰማያዊ ህንጻ ምድር ቢሮ ቁጥር 113

ስልክ ቁጥር፡-0116-630857

ፋክስ ቁጥር፡- 0116-623924

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 29 ቀን 2012
Deadline: June 22, 2020


© walia tender

Report Page