Binyam Esayas
#Update
ተማሪ ቢንያም ኢሳያስ እንዲሁም አባቱ ኢሳያስ ገ/ወልድ እንዲሁም የቤተሰቡ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ አያሌድ ቢታኔ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅን ውሳኔ እንደማይቀበለቱ ገለፁ።
ዩኒቨርሲቲውን ውሳኔውን እንዲቀለብስ እና ተማሪ ቢንያምን ከ4 ዓመት በላይ ወደለፋትበት የትምህርት ገበታው እንዲመልሰው ጠይቀዋል።
ይህንን የጠየቁት " ሸገር ኢንፎ " በሚሰኝ የዩትዩብ ገፅ ላይ በቀረቡበት ወቅት ነው።
የተማሪ ወላጅ አባት አቶ ኢሳያስ " ውሳኔው ተቀባይነት አለው ብዬ አላስብም ፤ በውሳኔው አዝኛለሁ አልቀበለውም፤ ውሳኔውን ተመልሰው እንዲያጤኑት " ሲሉ ጠይቀዋል።
" በሌላ ዓለም እንክብካቤ እየተደረገ እውቀት ያለው ጭንቅላት ያለውን ኡፍኡፍ እያሉ ነው የሚይዙት እዚህ ሳየው ተቃራኒ ሆኖብኛል " ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ኢሳያስ ልጃቸው ወደፊት ትልቅ ደረጃ ደርሶ የህዝቡ አገልጋይ ሆኖ እንደሚመጣ ምንም ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል።
ተማሪ ቢንያም በበኩሉ ፤ ውሳኔው ከዚህ በፊት ከነበረው ያልተለየ መሆኑን ገልጾ " በእነሱ ምክንያት ሀገሪቱ እየከሰረች ነው " ሲል ገልጿል።
" እኔ ፕሮሰሱን ጠብቄ ነው የገባሁት እኔ ባላጠፋሁት ምን አይነት ኃላፊነት እንደወሰዱ አልገባኝም ፤ እኔን ማብቃ ነው የሚገባቸው እንጂ ቴክኒካል ጉዳዮችን ጠቅሰው መናገራቸው ሲሉት የነበሩትን ነው የደገሙት ለእኔ የተለየ ውሳኔ አይደለም፤ የተለየ ውሳኔም አልጠበኩም ግልፅ ነው " ብሏል።
ተማሪ ቢንያም ዩኒቨርሲቲው የለፋበትን ትምህርት ሊያስጨርሰው እንደሚገባ ገልጾ በሌላ ዓለም ላይ ያሉ ተሞክሮዎችን መውሰድ ይቻላል ብሏል።
" የውጪዎቹ መጀመሪያ criteria አውጥተው አብቅተዋቸዋል ለህክምና እነዚህ ግን ይሄን ያህል ከተማርኩ በኃላ እዚህ ድረስ አድርሰውኝ እኔን ማብቃት ካልቻሉ Disabled የሆኑት እነሱ ናቸው " ሲል በስሜት ተናግሯል።
ይህንን ጉዳይ ለመከታተል #በነፃ በህግ አማካሪነት እና ጠበቃነት ከቤተሰቡ ጋር የቆመው አያሌው ቢታኔ ፤ ዩኒቨርሲቲው ኃላፊነት ወስጃለሁ ማለቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ውጤቱ ሙሉ ተጠያቂ ነኝ ማለት ነው። ከድርጊት እስከ ውጤት የኔ ጥፋት ነው በዚህ ለሚመጣው ማንኛውም ውጤት እቀበላለሁ ማለት ነው ስለዚህ ለውጤቱም መዘጋጀት አለባቸው ብለዋል።
ጉዳዩ የአንድ ቢንያም ብቻ አይደለም " በሀገራችን ከ18% በላይ Disabled የሆኑ ወንድም እህቶቻችን አሉ የእነዚህን የእያንዳንዱን ህይወት ነው የነጠቀው ውሳኔው፤ ውሳኔድ ከ18% በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያንን መብት ነው የነጠቀው የመማር መብታቸውን ነው የገረሰሰው ፣ ሞያቸውን የመምረጥ መብት ነው የገረሰሰው " ብለዋል።
" በዚህ ውሳኔ ላይ ድርሻህን የተወጣህ ቤትህ ይመጣልሃል ፤ነገ ተመሳሳይ አካል ጉዳተኛ ልጅ ወይም ከዚህ የባሰ ልጅ ስላለመውለድህ ማረጋገጫ የለህም ይህን ውሳኔ በልጅህ ላይ ትወስናለህ ? " ሲሉም ጠይቀዋል።
ውሳኔው ነገ የሌሎችን በር የሚዘጋ ና ሚዲያውን እና ህዝቡን የሚያሳስት በማር የተለወሰ መርዝ ነው ሲሉም ገልፀዋል።
እንደሱ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ በቅርቡ የሚመረቁ አሉ እዛው ግቢ ውስጥ ይህንን ከፕሬዜዳንቱ ጀምሮ ያውቃላ ለዚህ በቂ መረጃ አለን ብለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃም ልክ እንደሱ ሆነው የበቁ አሉ ማስረጃም ማቅረብ ይቻላል ሲሉ ገልፀዋል።
በቀጣይ አስፈፃሚው አካል የኮሌጁን ውሳኔ ላይ ከደመደመ ማስረጃ በማሰባሰብ ወደ ክስ እንገባለን ሲሉም አሳውቀዋል።