Audit oromia hibres sira...

Audit oromia hibres sira...


በድጋሚ የወጣ የሒሣብ ምርመራ ጨረታ ማስታወቂያ

የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያላቸውን የሒሣብ መርማሪ ድርጅቶችን (የኦዲት ድርጅቶችን) አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ስለሚፈልግ፤ኦሮሚያ ልዩ ዞን ስገላን ከተማ የሚገኘውን የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን ኃ/የተ/ የ2011 ዓ.ም ሒሳብ በውጪ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር (ኦዲት) ማስደረግ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በዚህ የሥራ መስክ ፈቃድ ያላቸውንና በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ሁሉ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

በጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ ሣር ቤት በሚገኘው ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ቢሮዎች ግቢ ውስጥ ከኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር አጋር የሥራ ሂደት ቀርበው የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ) በመክፈል መወሰድ ይችላሉ፣
ተጫራቾች ሒሣቡን ለመመርመር የሚያስከፍሉትን ዋጋ መጠንና ሥራውን ጀምረው የሚያጠናቅቁበትን የጊዜ ሠሌዳ ከጨረታው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
ተጫራቾች ከሚመለከተው መ/ቤት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፤ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
የሒሳብ ምርመራውን ሪፖርት በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጽ/ቤቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ማለት ም አስራ አንደኛው የሥራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 4 ፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ኤጀንሲው ለሥራው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች በሕብረት ሥራ ማሕበራት የሂሳብ ምርመራ ልምድ ያላቸውና በክልሉ የሥራ ቋንቋ በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጀውን መተዳደሪያ ደንብ፤ ቃለ ጉባኤዎች፤ የሂሳብ መዛግብቶችንና ሰነዶችን ማንበብና መረዳት የሚችሉ መሆን አለባቸው::
ስልክ ቁጥር፡- 0118 68 59 28 ፤ 0942 17 86 19

የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ



Posted:አዲስ ዘመን ግንቦት 09 ቀን 2012

Deadline: May 29, 2020


© walia tender

Report Page